በአዲስ አበባ ለሚካሄዱት የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ እና ለአፍሪካ – ጣልያን ጉባኤ በቂ ዝግጅት መደረጉን የመንግስት ኮምኒኬሽን አገልግሎት ገለፀ
በመዲናይቱ ለሚደረጉት አህጉር አቀፍ ጉባኤዎች ሆቴሎች እና የታክሲ አሽከርካሪዎች ለእንግዶች በቂ መረጃ እንዲሰጡ የሚያስችል ስልጠና ተሰቷቸዋል ሲል የመንግስት ኮምኒኬሽን አገልግሎት ተናገረ
ሰሞንኛ ሁነቶችን አሰመልክቶ ሲደረጉ የነበሩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ጨምሮ ተያያዥ ጉዳዩች ዙሪያ በዛሬዉ እለት የመንግስት ኮምኒኬሽን አገልግሎት በዋና መስሪያ ቤቱ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥቷል።
መግለጫዉን የሰጡት የመንግስት ኮምኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታዉ አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ በመዲናይቱ ሁለት ትልልቅ ጉባኤዎችን ማስተናገዷን አስመልክቶ የቅድመ ዝግጅቶች ስራዎችን አብራርተዋል።
ከአፍሪካ ህብረት ጉባኤ እና የአፍሪካ – ጣሊያን ጉባኤ መካሄድን ተከትሎ በከተማ ላይ የሚፈጠሩ መስተጓጎሎችን ነዋሪዎች የጉባኤው መካሄድ ከሚያስገኛቸዉ ጥቅም አንፃር የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ሲሉ ተናግረዋል።
እነዚህን ጉባዔዎች ለመዘገብ ከ800 በላይ የሚዲያ ባለሞያዎች ፈቃድ ጠይቀዋል ተብሏል።
ከ180 በላይ በሁሉም የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋዎች ብቁ የሆኑ የበጎ ፈቃድ ካዴቶች መሰረታዊ ሥልጠና ወስደው ተሰማርተዋል እንደሚገኙ አገልገሎቱ ገልፆል።
የቪዛ፣ የጉምሩክና የሚዲያ ፈቃድ አገልግሎቶችን በተመለከተ ሁሉም የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ያሉበት ፖርታል ተዘጋጅቶ የሰው ንክኪ በቀነሰ መልኩ በኦንላይን ስለሚከናወኑ አቶ ተስፋሁን ተናግረዋል።
ቁምነገር አየለ
የካቲት 05/2018 ዓ.ም
