የአሰልጣኞች ስንብት ቀጥሏል

ኖቲንግሃም ፎረስት በሃላፊነት ላይ ለ114 ቀናት ብቻ የቆዩትን ዋና አሰልጣኝ ሾን ዳይችን ከአሰልጣኝነት አሰናብቷል።

ክለቡ በዚህ የውድድር ዘመን ለአራተኛ ጊዜ አዲስ አሰልጣኝ ለመቅጠር ፍለጋ ላይ ይገኛል።

ፎረስት ትናንት ምሽት በሜዳው በደረጃው ግርጌ ላይ ከሚገኘው ዎልቭስ ጋር ያለምንም ግብ አቻ ከተለያየ በኋላ ከወራጅ ቀጠናው በ3 ነጥብ ብቻ ርቆ ይገኛል።

ሊጉ ሊጠናቀቅ ደግሞ 12 ጨዋታዎች ብቻ ቀርተዋል።

የ54 ዓመቱ ዳይች ባለፈው ጥቅምት ወር አንዤ ፖስቴኮግሉን ተክተው ሃላፊነቱን የያዙ ሲሆን፥ እስከ 2027 ክረምት ድረስ የሚቆይ ውል ፈርመው ነበር።

ክለቡ ከስንብታቸው በኋላ ባወጣው መግለጫ፤

“ኖቲንግሃም ፎረስት ሾን ዳይችን ከዋና አሰልጣኝነት ኃላፊነታቸው መነሳታቸውን ያረጋግጣል። ሾን እና ባልደረቦቻቸው በክለቡ በቆዩበት ጊዜ ላደረጉት ጥረት እናመሰግናለን፤ ለወደፊት ህይወታቸውም መልካም እድል እንመኛለን። ለጊዜው ከዚህ በላይ የምንሰጠው ተጨማሪ አስተያየት የለም” ብሏል።

ምስጋናው ታደሰ

የካቲት 05/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *