በሶማሌ ክልል ከ940 ሚሊዮን ብር በላይ የተገነቡ አራት የፀሃይ ኃይል ፕሮጀክቶች ተመረቀው 24 ሰዓት አገልግሎት መሰጠት ጀምረዋል፡፡
በሶማሌ ክልል ስምንት የፀሀይ ሀይል ማመንጫ ጣቢያዎች አገልግሎት ላይ ናቸዉ ተባለ
በሀገር አቀፍ ደረጃ ሰላሳ ስምንት የፀሀይ ሀይል ማመንጫ ኘሮጀክቶች አገልግሎት ላይ መሆናቸዉ ተናግሯል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለኢትዩ ኤፌም በላከዉ መግለጫ በዛሬዉ እለት በሶማሌ ክልል በዲግ፣ በኑስደሪቅ፣ በጋሻሞ እና በምርቃን የተገነቡት እነዚህ የጸሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች መመረቃቸዉን ገልፆል።
እነዚህ የፀሀይ ሀይል ማመንጫ ኘሮጀክቶች 1ነጥብ 8 ሜጋ ዋት ኃይል አጠቃላይ የማመንጨት አቅም ያላቸዉ ስለመሆኑ መግለጫዉ አትቷል።
ሙሉ በሙሉ ወጪዉ የአለም ባንክ የሸፈነባቸዉ እነዚህ ኘሮጀክቶች ከ940 ሚሊዮን ብር በላይ በማዉጣት የተገነቡ ስለመሆናቸዉ ነዉ አገልግሎቱ የገለፀዉ።
ኘሮጀክቶቹ በጤና እና በትምህርት ተቋማት ከ9 ሺ 500 በላይ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ የሚያደርጉ እንዲሆን የታለመ ነዉ ተብሏል።
ለፕሮጀክቶቹ ግንባታ 20 ነጥብ 42 ኪ.ሜ የመካከለኛ መስመር ዝርጋታ የተደረገለት መሆኑን በመግለጫዉ አስፍሯል።
በተያያዘም 78 ነጥብ 46 ኪ.ሜ ዝቅተኛ መስመር ዝርጋታ እንዲሁም 21 የተለያዩ አቅም ያላቸው ትራንስፎርመሮች ስለመተከላቸዉ አገልግሎቱ ለጣቢያችን ከላከዉ መግለጫ ለማወቅ ተችሏል።
በአሁን ወቅት በአገር አቀፍ ደረጃ 38 የጸሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ሙሉ በሙሉ ተጠናቀው አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙ ሲሆን፤ በሶማሌ ክልል ብቻ 8 የፀሀይ ኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች ለህብረተሰቡ አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ፡፡
የካቲት 09/2018 ዓ.ም
