ሁለቱም ወገኖች ለመሪዎቻቸው መረጃ ለመስጠት እና ስምምነት ላይ ለመድረስ መስራታቸውን ለመቀጠል ተስማምተዋል ሲሉ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ስቲቭ ዊትኮፍ ተናግረዋል፡፡
ልዩ መልዕክተኛዉ እንደገለጹት፤ዩክሬን እና ሩሲያ በጄኔቫ ከተካሄደው ሦስተኛው ዙር የሦስትዮሽ ውይይት በኋላ ድርድሩን ለመቀጠል ተስማምተዋል።
በፕሬዝዳንት ትራምፕ መሪነት፤ ዩናይትድ ስቴትስ ከዩክሬን እና ከሩሲያ ጋር የተካሄደውን ሦስተኛውን ዙር የሦስትዮሽ ውይይት አሸማግላለች ሲሉ በኤክስ ገጻቸው ላይ ገልጸዋል።
ዊትኮፍ ስዊዘርላንድ ስብሰባዎቹን ስላስተናገደችም አመስግነዋል።
ሁለቱም ወገኖች ለመሪዎቻቸው መረጃ ለመስጠት እና ስምምነት ላይ ለመድረስ መስራታቸውን ለመቀጠል ተስማምተዋል ሲሉ አክለዋል።
መልዕክተኛው ይህንን ያሉት በዩናይትድ ስቴትስ አሸማጋይነት በሩሲያ እና በዩክሬን ልዑካን መካከል የተጀመረው የመጀመሪያ ቀን የሰላም ድርድር ምንም ዓይነት ጉልህ ለውጥ ሳይታይበት መጠናቀቁን ተከትሎ ነው።
ዩናይትድ ስቴትስ በውይይቱ የተወከለችው በዊትኮፍ እና በፕሬዝዳንት ትራምፕ አማች ጃሬድ ኩሽነር ሲሆን፤ ኩሽነር ወደዚህ ድርድር የተቀላቀሉት ማክሰኞ ረፋድ በስዊዘርላንድ ከተማ በሌላ ቦታ ከኢራን ባለሥልጣናት ጋር ሲደረግ የነበረውን በተዘዋዋሪ መንገድ የሚካሄድ ውይይት ካገዙ በኋላ መሆኑን አናዶሉ ዘግቧል።
እስከዳር ግርማ
የካቲት 11/2018 ዓ.ም
