የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ፓሊስ መምሪያ በተለያዩ ጊዜያት ከወንጀል ፈፃሚዎች ላይ በኤግዚቢትነት የያዛቸውን ከ 80 ኪሎ ግራም በላይ ካናቢስ የተባለ አደንዛዥ ዕፅ ሌሎች አደንዛዥ ዕፆችን በአንድ ላይ አስወግዷል።
ዕፆቹ ፓሊስ በተለያዩ ጊዜያት በአዘዋዋሪዎችና በተጠቃሚዎች ላይ በወሰደው ጠንካራ የክትትል ስራ በቁጥጥር ስር የዋሉ መሆናቸውን የገለፁት የፓሊስ መምሪያው የኤግዚቢት ክፍል ኃላፊ ኮማንደር ሲሳይ አበራ የካናቢስ አደንዛዥ ዕፅን ጨምሮ በመድኃኒት መልክ የሚወሰዱ አደንዛዥ ዕፆችና የሺሻ ማስጨሻ ቁሳቁሶች መወገዳቸውን ገልፀዋል።
ኮማንደር ሲሳይ አበራ አያይዘውም የተወገዱት አደንዛዥ ዕፆች ጥቅም ላይ ቢውሉ በማህበረሰቡ ላይ በተለይም በታዳጊዎች ላይ የከፋ አካላዊና ስነ-ልቦናዊ ጉዳት የሚያደርሱ መሆናቸውን በመግለፅ ማህበረሰቡ ይህን በመረዳት መሰል ድርጊቶችን የሚፈፅሙ አካላትን ለህግ ሊያቀርቡ እንደሚገባ መልዕክት አስተላልፈዋል ።
የካቲት 12/2018 ዓ.ም
