ለምግብና ለመጠለያ ሲል ራሱን ያሳሰረው ሩሲያዊ

​በሩሲያ ባሽኮርቶስታን ግዛት የሚኖረውና በ20ዎቹ ዕድሜ ውስጥ የሚገኘው “ኦሌግ”፣ ሥራ አጥቶ መኖር ስለከበደው ለመታሰር ወስኗል።

ኦሌግ ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከተመረቀ በኋላ በወታደራዊ አገልግሎት ውስጥ የቆየ ሲሆን፣ በቅርቡ በሩሲያዋ ኡፋ ከተማ ውስጥ ሥራ ለመቀጠር ተደጋጋሚ ሙከራዎችን ቢያደርግም አልተሳካለትም ነበር።

የሚኖርበት ቦታና የሚቀመስ ምግብ ያጣው ይህ ወጣት፣ መጨረሻ ላይ ተስፋ በመቁረጥ ራሱን ወደ እስር ቤት ለማስገባት የሚያስችል እቅድ አወጣ።

​ኦሌግ መጀመሪያ  ያደረገው ነገር በአንድ ሆቴል ውስጥ ገብቶ “ቦምብ አለኝ” ብሎ ማስፈራራት ነበር ነገር ግን ማንም ሳያምነው በመቅረቱ ሀሳቡ ሳይሳካ ይቀራል።

በመቀጠልም ወደ ኡፋ አውሮፕላን ማረፊያ በመሄድ ቦርሳውን ከፍ አድርጎ “ቦምብ ላፈነዳ ነው” በማለት ጮኸ ፤በዚህ ተግባሩ ግን በፖሊሶች ቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል።

ጉዳዮ ሲጣራም ምንም ዓይነት ፈንጂ እንዳልነበረው እና ድርጊቱን የፈጸመው ሆን ብሎ ለመታሰር እንደሆነ አመነ።

ፖሊሶቹም ​የአእምሮ ጤንነቱን አረጋግጠው ጤነኛ መሆኑ ከታወቀ በኋላ ለፍርድ እንዲቀርብ አድርገውታል።

ኦሌግ የሕዝብን ሰላም በማናጋት ወንጀል ተከሶ የሦስት ዓመት ከሁለት ወር እስራትም ተፈርዶበታል።

በዚህም ምክንያት እንደፈለገው መጠለያና በቀን ሁለት ጊዜ የሚቀርብ ምግብ ማግኘት ችሏል ሲል ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል ።

ሐመረ ፍሬው

የካቲት 13/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *