ሶማሊላንድ እውቅና ለማግኘት በምታደርገዉ ጥረት ለአሜሪካ የማዕድን ቁፋሮ ዕድል እንደምትሰጥ ገለጸች

ሶማሊላንድ ዓለም አቀፍ እውቅና ለማግኘት የምታደርገውን ጥረት በመቀጠል፤ ለአሜሪካ የማዕድን ሀብቶቿን እና የወታደራዊ ካምፖቿን የመጠቀም ዕድል ለመስጠት ፈቃደኛ መሆኗን አስታውቃለች።

ሶማሊላንድ በ1991 ከሶማሊያ መገንጠሏን ካወጀች በኋላ እስራኤል የክልሉን ነፃነት እውቅና የሰጠች የመጀመሪያዋ እና ብቸኛዋ ሀገር ሆናለች።

የሶማሊላንድ የፕሬዚዳንት ቢሮ ሚኒስትር ኻዳር ሁሴን አብዲ፤ ‹‹ጓደኞቻችን እስራኤልም ሆኑ አሜሪካ፤ ያሉንን የማዕድን እምቅ አቅሞች በተለይም ለአሜሪካ በጣም አስፈላጊ እየሆኑ የመጡትን ብርቅዬ ማዕድናትን እንዲመረምሩ እንፈልጋለን››ብለዋል።

ከኤኤፍፒ የዜና ወኪል ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፤ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር በአንድ ስምምነት ላይ እንደምንደርስ አዉቃለሁ ሲሉ ገልጸዋል።

ምንም እንኳን እስካሁን በገለልተኛ አካል የተረጋገጠ ማስረጃ ባይኖርም፤የግዛቱ ተፈጥሮዓዊ ሀብቶች ሊቲየም፣ ኮልታን እና ሌሎች ተፈላጊ ቁሳቁሶችን ያካትታሉ፡፡

ባለፉት ጥቂት ሳምንታት የሶማሊላንድ መሪ አብዲራህማን መሐመድ አብዱላሂ፤ ለእስራኤል የማዕድን ሀብቶች ልዩ የመጠቀም ዕድል ለመስጠት ሐሳብ አቅርበው ነበር።

ክልሉን የሶማሊያ አካል አድርጋ የምትቆጥረው ሞቃዲሾ፤ የእስራኤልን እውቅና በግዛታዊ አንድነቷ ላይ የተሰነዘረ ጥቃት በማለት አውግዛለች፤ ይህ አቋም በአብዛኞቹ የአፍሪካ እና የአረብ መሪዎች የተደገፈ ነው።

ተንታኞች እንደሚጠቁሙት፤እስራኤል ለሶማሊላንድ እውቅና የሰጠችው ከየመን ማዶ ባለው የኤደን ባህረ ሰላጤ ላይ ባላት ስልታዊ መገኛ ምክንያት ነው።

የየመን አማፂያን ሁቲዎች ከፍልስጤማውያን ጋር ያላቸውን አብሮነት ለመግለጽ፤ በአካባቢው በሚገኙ የእስራኤል ንብረቶች ላይ በተደጋጋሚ ጥቃት ሲሰነዝሩ ቆይተዋል።

ባለስልጣናቱ፤የሶማሊላንድ ተቀባይነት ‹‹በወታደራዊ ወይም በፀጥታ ጉዳዮች የተመሰረተ ሳይሆን፤እስራኤል ያለን ነባር መንግሥት እውቅና በመስጠቷ ነው›› ብለዋል።

እስከዳር ግርማ

የካቲት 16/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *