አብዛኞቹ ኢንተርፕራይዞች የደረጃ ሽግግር ለማድረግ ፍላጎት እንደማያሳዩ ተነገረ

በኢትዮጵያ ያሉ ከጥቃቅን ወደ አነስተኛ ከአነስተኛም ወደ ከፍተኛ ኢንተርፕራይዝ የደረጃ ሽግግር ማድረግ የማይፈልጉ ኢንተርፕራይዞች እንዳሉ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ነግሮናል።

ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት በኢትዮጵያ የኢንተርፕራይዝ ልማት የህዝብ ግንኙነት እና የኮሚኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ አቶ ሮቤል አህመድ፤ ለሽግግር ፍላጎት የማያሳዩበትን ምክንያት ገልፀዋል።

አቶ ሮቤል ኢንተርፕራይዞቹ ሽግግር ሲያደርጉ በነበሩበት ደረጃ ሲሰጣቸዉ የነበረዉ ድጋፍ ይቆማል ወይም ይቀንሳል ብለዉ ስጋት ዉስጥ እንደሚገቡ ነግረዉናል።

ለአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የስራ ማስኬጃ ብድርን ጨምሮ አቅም ለመገንባት በሚደረገዉ ስራ ለኢንተርፕራይዞች የደረጃ ሽግግር ዙሪያ የነበሩ ክፍተቶችን ለመሙላት የሽግግር ስትራቴጂ እና ማንዋል መዘጋጀቱን ሰምተናል።

በሽግግር ስትራቴጂ ማንዋል የትኛዉ ኢንተርፕራይዝ ባለበት እና በሚደርስበት ደረጃ ያስፈልገዋል የሚለዉን ድጋፍ አብራርቶ የሚያስቀምጥ መሆኑ ተገልጿል።

በፌዴራል ደረጃ የተዘጋጀው ማንዋሉ ክልሎች በራሳቸዉ ተጨባጭ ሁኔታ እንዲመሩበት የሚደረግ መሆኑን የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የህዝብ ግንኙነት እና የኮምኒኬሽን ስራ አስፈፃሚዉ አቶ ሮቤል አህመድ ተናግረዋል።

ወደ 1 ሺህ 1መቶ67 የሚሆኑ ኢንተርፕራይዞች ወደ 3.6 ቢሊየን የሚጠጋ የስራ ማስኬጃ ብድር እንዲያገኙ የታቀደበት የባለፉት ስድስት ወራት 9 መቶ 90 አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ወደ 7 ቢሊየን የሚጠጋ የስራ ማስኬጃ ብድር ወስደዋል ተብሏል።

ቁምነገር አየለ

የካቲት 17/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *