የሴኔጋል ጠቅላይ ሚኒስትር በተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ላይ የሚጣለውን ቅጣት ለመጨመር ቃል ገቡ

የሴኔጋል ጠቅላይ ሚኒስትር ኡስማን ሶንኮ፤ በተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ላይ የሚጣለውን ከፍተኛ ቅጣት እስከ አስር ዓመት እስራት የሚያደርስ ረቂቅ ሕግ ይፋ አድርገዋል።

ይህ ረቂቅ ሕግ ‹‹ለተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ቅስቀሳ በሚያደርግ›› ማንኛውም ሰው ላይ ከሶስት እስከ ሰባት ዓመት የሚደርስ እስራት ይጥላል።

ኡስማን ሶንኮ ለፓርላማው ሲናገሩ ማንኛውም ‹‹ከተፈጥሮ ውጪ የሆነ ድርጊት›› የሚፈጽም ሰው ከአምስት እስከ 10 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት ይቀጣል ብለዋል።

በተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት የተጠረጠሩ ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋልን ተከትሎ፤ ሚኒስትሮች ረቂቅ ሕጉን ባለፈው ሳምንት ለፓርላማው መርተውታል።

በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል ሁለት የአገር ውስጥ ታዋቂ ሰዎችና አንድ የታወቀ ጋዜጠኛ ይገኙበታል።

ይህ ውሳኔ የመጣው ባለፉት ጥቂት ዓመታት የሃይማኖት ድርጅቶች ጠንከር ያለ ቅጣት እንዲጣል በመጠየቅ ተቃውሞ ሲያደርጉ ከቆዩ በኋላ ነው።

በፓርላማው ድምጽ የሚሰጥበት ቀን እስካሁን አልተቆረጠም ያለዉ አፍሪካ ኒዉስ ነዉ።

እስከዳር ግርማ

የካቲት 18/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *