የፌስቱላ ህመም የሚያደርሰዉን የስነልቦና እና ማህበራዊ ጫና ለመቀነስ ስራዎች እየሰራ መሆኑን ሀምሊን ፌስቱላ ገለፀ

ከፊስቱላ ህክምና በኋላ እናቶችን በኢኮኖሚ የማቋቋምና ወደ ማህበረሰቡ የመቀላቀል ስራዎች ተጠናክረው ቀጥለዋል ተብሏል።

የፊስቱላ ህመም የገጠማቸው እናቶች ከህክምናው ባሻገር ከሚደርስባቸው ስነ-ልቦናዊና ማህበራዊ ጫና አገግመው ራሳቸውን እንዲችሉ የማድረግ ስራ አበረታች ውጤት እያመጣ መሆኑ ተገልጿል።

የሀምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር ቢንያም ሲራክ፤ የፊስቱላ ህመም ምክንያት እናቶችን ከማህበረሰቡ እንዲገለሉ፣ ትዳራቸው እንዲፈርስና ለከፍተኛ የኢኮኖሚና የስነ-ልቦና ችግር እንዲዳረጉ ማድረጉን ገልፀዋል።

ይህንን ችግር ለመፍታት ተቋሙ “ደስታ መንደር” በተሰኘው የማገገሚያ ማዕከሉ በዓመት እስከ 1 ሺህ 5መቶ ለሚደርሱ እናቶች የስነ-ልቦና ድጋፍና የክህሎት ስልጠናዎችን ይሰጣል ብለዋል።

እናቶቹ በቆይታቸው እንደ ልብስ ስፌት፣ የሸክላ ስራ፣ ዳቦ መጋገር፣ የዶሮ እርባታ እና የመሳሰሉትን የገቢ ማስገኛ ሙያዎች እየሰለጠኑ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

ስልጠናቸውን ሲያጠናቅቁም ተቋሙ የስራ መነሻ ድጋፍ በማድረግ እና አስፈላጊ ቁሳቁሶችን በማሟላት ወደ ማህበረሰባቸው ተመልሰው ራሳቸውን ችለው በክብር እንዲኖሩ የማድረግ ስራ እየሰራ እንደሚገኝ አብራርተዋል።

ሊዲያ ደሳለኝ

የካቲት 26/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *