ዶናልድ ትራምፕ በኋይት ሀውስ በተካሄደ አንድ ዝግጅት ላይ እንደተናገሩት አሜሪካ የኢራንን የድሮን እና የሚሳኤል ስርዓቶች በየሰዓቱ እየመታች ሲሆን፣ የእስራኤል ጦር አዛዥ በበኩላቸው ሀገሪቱ ወደ ቀጣዩ የጦርነት ምዕራፍ እየተሸጋገረች መሆኑን ገልጸዋል።
የአሜሪካ እና የእስራኤል ጥቃት በኢራን ላይ ለ7 ቀን በቀጠለበት በዚህ ወቅት፣ የኢራን ነዋሪዎች ለቢቢሲ በሰጡት ቃል ሕይወት እጅግ አድካሚ እንደሆነችና ወጥመድ ውስጥ እንደገቡ እንደሚሰማቸው ተናግረዋል።
አንድ ነዋሪም ጥቃቱ ቤቱን በሚያናውጥበት ወቅት ሁኔታው እጅግ አስፈሪ እንደሆነ ጠቅሷል።
በሌላ በኩል የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ስድስት የኢራን ሚሳኤሎችን እና 131 ድሮኖችን ማክሸፏን ተከትሎ፣ የሀገሪቱ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ነዋሪዎች መጠለያ እንዲፈልጉ የሚያሳስብ የአስቸኳይ ጊዜ ማስጠንቀቂያ አውጥቷል።
የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ሰር ኬር ስታርመርም አራት ተዋጊ ጄቶችን ወደ ኳታር እንደሚልኩ አስታውቀዋል እንደ ቢቢሲ ዘገባ።
ሐመረ ፍሬው
የካቲት 27/2018 ዓ.ም
