ይህንን ያለዉ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ሲሆን፤ ተቋሙ ኢንተርፕራይዞችን የግብዓት እና የፋይናንስ ችግሮች ያሉባቸዉ መሆኑን ገልጿል።
ከኢትዮ ኤፍ ኤም ጋር ቆይታ ያደረጉት የተቋሙ የኮሚኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ አቶ ሮቤል አህመድ፤ ስራ እንዲጀምሩ የተደረጉት 47ቱ አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች እንዲሁም 35ቱ መካከለኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ መሆናቸዉን ተናግረዋል።
ከእነዚህ ኢንተርፕራይዞች አብዛኞቹ በኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦት እና በግብዓት ችግር ስራ እንዳቆሙ አቶ ሮቤል ነግረዉናል።
የኢንተርፕራይዞቹን የሀይል አቅርቦት በተመለከተ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ጋር እየሰራን እንገኛለን ሲሉ ተናግረዋል።
አቶ ሮቤል ለኢንተርኘራይዞች የሊዝ ፋይናንስ ወይም የማሽን አቅርቦት አሰራር እንዳለ ይናገራሉ።
ለዚህ አሰራር እንዲያመችም በየክልሎቹ ተቋማት እንዲኖሩ መደረጉን ተናግረዉ፤ከጉዳዩ ጋር ተያይዞ የሊዝ ፋይናንስ አዋጁም እንዲሻሻል ተቋሙ እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
የኢንተርፕራይዞች ፈተና የሆነዉ የግብዓት አቅርቦትን በተመለከተ የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት(ኢግልድ) ጨምሮ ሌሎች አለምአቀፍ ተቋማት ይህንን የግብዓት አቅርቦት እንዲፈቱ የተመረጡ ተቋማት አሉ ተብሏል።
2 ሺህ 3 መቶ የሚጠጉ ኢንተርፕራይዞች በ6 ወራቱ የግብዓት አቅርቦት እንዲያገኙ ስለመደረጉ አቶ ሮቤል አህመድ ተናገረዋል።
ኢንተርፕራይዞች ከዉጭ ንግድ አንፃር 63 ኢንተርፕራይዞች ምርታቸዉን ለዉጪ ንግድ ገበያ መላክ መቻላቸዉን ሰምተናል።
የጨርቃጨርቅ ኢንተርፕራይዞች ለዉጪ ንግድ ከፍተኛ ድርሻ ኖሯቸዉ ምርታቸዉን ስለማቅረባቸው የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ተናግሯል።
ሀና ሰይፉ
የካቲት 27/2018 ዓ.ም
