እስራኤል ጥቃቷን ማጠናከሯን ተከትሎ በሊባኖስ ከ5መቶ ሺህ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸዉ ተገለጸ

የሊባኖስ የማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፤ባለፈው ሳምንት ግጭቱ ዳግም ካገረሸ ወዲህ 5መቶ17 ሺህ ሰዎች ተፈናቃይ ሆነው ተመዝግበዋል ብሏል።

የሊባኖስ የማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ሃኒን ሰይድ በሰጡት መግለጫ፤የሚኒስቴሩ ድረ-ገጽ ላይ የተመዘገቡት ተፈናቃዮች ቁጥር 5መቶ17 ሺህ ደርሷል፤ ከነዚህም ውስጥ 1መቶ17 ሺህ 2መቶ28 የሚሆኑት በመንግስት መጠለያዎች ውስጥ ይገኛሉ።

መግለጫው የተሰጠው እስራኤል በሊባኖስ የምታደርገውን ወታደራዊ ዘመቻ ባሰፋችበት እና ለመጀመሪያ ጊዜ የቤሩትን መሃል ከተማ በመታችበት ወቅት ነው።

የሊባኖስ የጤና ሚኒስቴር መረጃ እንደሚያሳየዉ፤ ባለፈው አንድ ሳምንት ውስጥ ብቻ በሊባኖስ 3መቶ94 ሰዎች የተገደሉ ሲሆን፤ከእነዚህም ውስጥ 83 ሕፃናት፣ 42 ሴቶች እና 9 የነፍስ አድን ሠራተኞች ይገኙበታል።

ሊዲያ ደሳለኝ

የካቲት 30/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *