ኢራን ጥቃቷን ለመቀጠል መዘጋጀቷንና ከአሜሪካ ጋር የሚደረግ ድርድር እንደማይኖር አስታወቀች

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ ሀገራቸው አስፈላጊ ሆኖ እስከተገኘ ድረስ የሚሳኤል ጥቃቶችን ለመቀጠል ዝግጁ መሆኗን ገልጸዋል።

ሚኒስትሩ ከአሜሪካ ጋር የሚደረግ ማንኛውም ዓይነት ድርድርም ከአጀንዳ ውጭ መሆኑን በይፋ አስታውቀዋል።

አባስ አራግቺ ለአሜሪካው ፒቢኤስ የዜና አውታር በሰጡት ቃለ ምልልስ፤ ኢራን ጥቃቷን ለመቀጠል ያላትን ቁርጠኝነት ገልጸው፤ ድርድርን በተመለከተ የቀረበውን አማራጭ ውድቅ አድርገዋል።

ይህ የኢራን መግለጫ የወጣው፣ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር ያለው ጦርነት “በጣም በቅርቡ” ያበቃል ካሉ በኋላ መሆኑ ተጠቁሟል።

ይሁን እንጂ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ንግግር የትራምፕን ግምት የሚያጣጥልና የሁለቱን ሀገራት ውጥረት ይበልጥ የሚያባብስ ሆኖ ተገኝቷል።

በአሁኑ ወቅት በኢራንና በአሜሪካ መካከል ያለው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ተቋርጦ የሚገኝ ሲሆን፤ የቀጣናው ስጋትም በከፍተኛ ሁኔታ እያየለ መምጣቱን የዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

ልዑል ወልዴ

መጋቢት 01/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *