የጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ደምና ሕብረ ሕዋስ ባንክ አገልግሎት “ጾም ለነፍስ፣ ደም ልገሳ ለሕይወት” በሚል መሪ ቃል በመጋቢት ወር የሚቆይ ብሔራዊ የደም ልገሳ ንቅናቄ በይፋ መጀመራቸውን አሳውቀዋል::
ባለፉት ስምንት ወራት 3 መቶ22ሺ3 መቶ55 ዩኒት ደም መሰብሰብ መቻሉ የተገለፀ ሲሆን፥ይህም ከታቀደው ግብ ውስጥ 88 በመቶው መሳካቱን ያሳያል ተብሏል።
በመጋቢት ወር አዲስ ንቅናቄ ተጨማሪ 40ሺ ዩኒት ደም ለመሰብሰብ መታቀዱም ተጠቁሟል።
በተጨማሪም ጾም ደም ለመለገስ እንቅፋት አለመሆኑንና ጾመኞች ማታ ምግብ ከተመገቡ በኋላ በመለገስ ሰብአዊ ተግባራቸውን መወጣት እንደሚችሉ የኢትዮጵያ ደም እና ህብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር አሸናፊ ታዘበው አስረድተዋል::
ዶ/ር አሸናፊ አክለውም ዕድሜያቸው ከ17 እስከ 65 የሆኑ እና ክብደታቸው ከ45 ኪሎ ግራም በላይ የሆኑ ዜጎች ሁሉ ደም በመለገስ የእናቶችንና የሕፃናትን ሕይወት እንዲታደጉ ጥሪ አቅርበዋል።
ሀና ሰይፉ
መጋቢት 04/2018 ዓ.ም
