ከሁለት ዓመታት በኋላ በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ይካሄዳል ተብሎ ለሚጠበቀው 32ኛው የአለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (COP 32) የኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የበኩላቸውን ሚና ለመወጣት ከወዲሁ ዝግጅት መጀመራቸው ተገለጸ።
የኢትዮጵያ ስነ-ተዋልዶ ጤና ሰጪ ድርጅቶች ህብረት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አበበ ከበደ፥ በዱባይ በተካሄደው ተመሳሳይ ጉባኤ ላይ የኢትዮጵያ መንግስት የራሱን ፓቪሊዮን አዘጋጅቶ የአገሪቱን የልማትና የአረንጓዴ አሻራ ስራዎች በስፋት ማስተዋወቅ ችሏል ብለዋል።
ይህን መልካም ተሞክሮ በመውሰድ አገር በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በኢትዮጵያ በሚካሄደው ጉባኤ ላይ ጠንካራ ተሳትፎ ለማድረግ አቅደዋል።
መንግስት የሚያስቀምጠውን አቅጣጫ መሰረት በማድረግ፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የአየር ንብረት ለውጥ በተለይም በሴቶችና ህፃናት ጤና ላይ እያደረሰ ያለውን ተጽዕኖ ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማሳየት እና ተገቢውን ድጋፍ ለማሰባሰብ የሚያስችላቸውን የጋራ ሰነድና አቋም ከወዲሁ እያዘጋጁ መሆኑ በጉባኤው ላይ ተብራርቷል።
ሊዲያ ደሳለኝ
መጋቢት 04/2018 ዓ.ም
