የአዕምሮ ጤና ህክምና በአማኑኤል ሆስፒታል ብቻ የሚሰጥ ህክምና መሆኑ ይታወቃል።
ህክምናዉ በአስገዳጅነት ከሆስፒታሉ ጥገኝነት ተላቅቆ በሁሉም ሆስፒታሎች መሰጠት መጀመሩን ሰምተናል።
ይህን የነገሩን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ወንደሰን በርሄ ናቸዉ፡፡
እንደ አስተባባሪዉ ገለፃ፤ከዚህ ቀደም ማንኛውም የአዕምሮ ጤና እክል ያጋጠመው ሰው ህክምና ለማግኘት የግድ ወደ አንድ ማዕከል ማለትም ወደ አማኑኤል ሆስፒታል ብቻ መሄድ ነበረበት ብለዋል።
ይህ ደግሞ በሆስፒታሉ ላይ ከፍተኛ ጫና ከመፍጠሩም በላይ፤ ታካሚዎች ህክምናውን በቀላሉ እንዳያገኙ እንቅፋት ሆኖ ቆይቷል።
ይህንን ስር የሰደደ ችግር ለመፍታት የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ በአሁኑ ሰዓት በሁሉም የመንግስት ሆስፒታሎች ውስጥ የአዕምሮ ጤና ባለሙያዎችን መድቧል።
በዚህም መሰረት ታካሚዎች ወደ አማኑኤል ሆስፒታል መሄድ ሳያስፈልጋቸው ሌሎች መደበኛ የህክምና አገልግሎቶችን በሚያገኙባቸው በአቅራቢያቸው ባሉ ሆስፒታሎች ውስጥ የተሟላ የአዕምሮ ጤና ህክምና አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ ተነግሯል።
ሊዲያ ደሳለኝ
መጋቢት 07/2018 ዓ.ም
