ኢራን የዓለም ዋንጫ ጨዋታዎቿን በሜክሲኮ ለማከናወን ጠየቀች

የኢራን የእግር ኳስ ማህበር ከደህንነት ጋር በተገናኘ ኢራን የዓለም ዋንጫ ጨዋታዎቿን በሜክሲኮ ማከናወን እንድትችል እንዲፈቅድላት ከፊፋ ጋር እየተደራደረ መሆኑን አሳውቋል።

የኢራን እግር ኳስ ማህበር ፕሬዝዳንት መህዲ ታጅ በኤክስ ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት “ትራምፕ ለኢራን ብሄራዊ ቡድን ደህንነት ማረጋገጫ እንደማይሰጥ ግልጽ ባደረገበት ሁኔታ ወደ አሜሪካ ልንጓዝ አንችልም” ብለዋል።

አያይዘውም ” ኢራን በዓለም ዋንጫ የምታደርጋቸውን ጨዋታዎች በሜክሲኮ ልታከናውን በምትችልበት መንገድ ዙሪያ ከፊፋ ጋር እየተነጋገርን ነው” ብለዋል።

ባለፈው ሳምንት የኢራን የስፖርት ሚኒሰትር አሜሪካና እስራኤል ጥቃት ከፈጸሙብን በኋላ በውድድሩ ላይ የመሳተፋችን ነገር የማይታሰብ ነው ማለታቸው ይታወሳል።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ “ኢራን በውድድሩ መሳተፍ ትችላለች። ለራሳቸው ደህንነትና ህይወት ሲሉ ግን ባይገኙ ይሻላል” ማለታቸው አይዘነጋም።

የኢራን ብሔራዊ ቡድን አስቀድሚ በተያዘው ፕሮግራም ሁለት የምድብ ጨዋታዎችን በሎስ አንጀለስ ፣ ቀሪውን አንድ ጨዋታ በሲያትል እንዲያከናውኑ ቀጠሮ ተይዟል።

አቤል ጀቤሳ

መጋቢት 08/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *