ጳጉሜን የገንዘብ ቁጠባና ብድር ማህበር ለአባላቱ የበዓል ዶሮን “በብድር” ሊያቀርብ ነው

ጳጉሜን የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ መሰረታዊ የኅብረት ሥራ ማህበር  መጪውን  በዓል  ምክንያት በማድረግ ለአባላቱ የዶሮ አቅርቦት እንዲመቻች ከተቋማት ጋር ስምምነት ማድረጉን ዛሬ መጋቢት 8 ቀን 2018 ዓ.ም በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል።

ማህበሩ አባላቱ የበዓል ወጪያቸው  ጫና እንዳይፈጥርባቸው ለማገዝ ከዶሮ አቅራቢ ተቋም ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል።

ይህ አቅርቦት አባላቱ የበዓል ፍጆታቸውን በብድር እንዲያገኙ የሚያስችልና ማህበራዊ ድጋፍን ታሳቢ ያደረገ መሆኑ ተገልጿል።

ከበዓል አቅርቦቱ በተጨማሪ፥አባላቱ የቤት ውስጥ የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁሶችን በብድርና በቅናሽ ዋጋ የሚያገኙበት አጋርነት ተፈጥሯል።

የማህበሩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ዘላለም ጌታነህ እንደተናገሩት፥ “ትልቅ ሀገር ይዘን ትንሽ አንሆንም” በሚል መሪ ቃል ማህበሩ እስከ 15 ሚሊየን ብር የሚደርስ የንግድ፣ የመኪና እና የቤት ብድሮችን እያቀረበ ይገኛል።

የብድር መክፈያ ጊዜውም እንደ አስፈላጊነቱ እስከ 10  ዓመት የሚቆይ ሲሆን፥የወለድ መጠኑም ከ14 በመቶ እስከ 18 በመቶ እንደሆነና ከወለድ ነፃ የሆኑ የቁጠባና ብድር አማራጮችም መኖራቸው ተጠቅሷል።

ዋና ስራ አስፈፃሚው አክለውም ማንኛውም ግለሰብ 2000 ብር የአገልግሎት ክፍያ በመክፈልና የ5000 ብር መነሻ ዕጣ በመግዛት አባል መሆን እንደሚችል ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም ማህበሩ አርቲስት ፍቃዱ ከበደን የብራንድ አምባሳደር  አድርጎ  ሾሟል፡፡

ሀና ሰይፉ

መጋቢት 08/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *