ከ400 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ግንባታ፣ ጥናት፣ዲዛይንና ኤሌክትሮ መካናኒክ እቃዎች አቅርቦት ውል ስምምነት ተፈረመ።

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በአማራ ፣በኦሮሚያ እና ጋምቤላ ክልሎች ከ400 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ግንባታ፣ ጥናት፣ዲዛይንና ኤሌክትሮ መካናኒክ እቃዎች አቅርቦት ከስምንት ድርጂቶች ጋር ውል ስምምነት ተፈራረመ።

ስምምነቱን የተፈራረሙት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ዶ/ር አስፋው ዲንጋሞ የህብረተሰቡን የመጠጥ ውሃ ችግር ለመቅረፍ በተገባው የውል ስምምነት መሰረት በሚፈለገው የጥራት ደረጃና በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ፕሮጀክቱን በማጠናቀቅ የህብረተሰቡ የመጠጥ ውሃ ችግር እንዲፈታ አሳስበዋል።

ፕሮጀክቶቹ በአራት ክልሎች እንደሚተገበሩ የገለጹት ክብር አምባሳደሩ ከ400 ሚሊዮን ብር በላይ ከመንግስት በተያዘ በጀት ስራው እንደሚከናወን ገልጸዋል፡፡

ፕሮጀክቱ የሚተገበርባቸው አካባቢዎች በአማራ ክልል መካነ ሰላም፣ሰቆጣ እና ገለሱት በኦሮሚያ ክልል ምእራብ ሸዋ ጀዱ ወረዳ ፣በትግራይ ክልል ማይጸብሪ ፣በጋምቤላ ክልል ሲሆኑ ድርቅ የሚያጠቃቸው አካባዎች በመሆናቸው ግንባታው በተያዘለት የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቅ በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በኩልም የተለመደው ድጋፍና ክትትል እንደሚደረግ ገልፀዋል፡፡

የግንባታ ፕሮከጅቶቹ በ6 ወር የጌዜ ገደብ የእቃ አቅርቦት የአንድ ወር እና ጉድጓድ ቁፋሮ በ3 ወር የጊዜ ገደብ ተጠናቀው ለአገልግሎት እንደሚበቁ ተገልጿል፡፡

መጋቢት 09/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *