10ኛው ኢትዮ ኸልዝ ዓለምአቀፍ አውደርዕይና ጉባኤ እንዲሁም 2ኛው የሀገር ውስጥ የህከምና ግብዓት ምርትና ኢኖቬሽን እግዚቢሽን በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር፣ በአርማወር ሀንሰን የምርምር አንስቲትዩት (AHRI) እና በፕራና ኢቨንትስ አዘጋጅነት እንደሚካሄድ ተገልጿል።
የዘንድሮው ኹነት ከ 8 ሀገራት የተውጣጡ ከ 90 በላይ ኩባንያዎች የሚሳተፉበት እንደሆነ ተነግሯል።
በተጨማሪም ከ40 በላይ የሙያ ማጎልበቻ (CPD) ስልጠናዎች፣ 3ኛው የዲጂታል ኸልዝ ሃካቶን እና ሳይንሳዊ ፎረሞች የኹነቱ አካል ነው ተብሏል።
አውደ ርዕዩ አዳዲስ ቴከኖሎጂዎችን እና አቅራቢዎችን ለሀገራችን በማስተዋወቅ፣ የቴከኖሎጂ እና የዕውቀት ሽግግርን በማምጣት ለዘርፉ ልማት በሚደረገው ጥረት ውስጥ ቁልፍ መድረከ እንደሆነም ተጠቁሟል።
እንዲሁም በዘርፉ ተዋናዮች መካከል የንግድ ልውውጥን በማሳደግ እና የገበያ ትስስርን የመፍጠር ዕድል እንዳለው ተነስቷል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ 2ኛው የሀገር ውስጥ የህከምና ግብዓት ምርትና ኢኖቬሽን ኤግዚቢሽን የሚካሄድ ሲሆን የሀገር ውስጥ የህከምና መሣሪያዎች፣ የመድኃኒት አምራቾች እና የጤና ቴክኖሎጂ ፈጠራዎችን ለማበረታታትና ለገበያ ለማቅረብ የሚረዳ መሆኑ ተገልጿል።
አውደ ርዕዩና ኤግዚቢሽኑ ከመጋቢት 24 እስከ 26 በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ሴንተር እንደሚካሄድም ተመላክቷል።
ሊዲያ ደሳለኝ
መጋቢት 09/2018 ዓ.ም
