በኬንያ ኬሪቾ ከተማ የተገኘው የጅምላ መቃብር በሀገሪቱ ከፍተኛ ድንጋጤን ፈጥሯል።

በኬንያ ኬሪቾ ከተማ በሚገኝ አንድ የጅምላ መቃብር ውስጥ የተገኙ አስከሬኖችን የማውጣት ሂደት የቀጠለ ሲሆን፣ እስካሁን በአብዛኛው ህፃናት የሆኑ 32 አስከሬኖች መገኘታቸው ተገልጿል።

ፖሊስ አስቀድሞ በቦታው ተቀብረዋል ተብሎ የታሰቡ 14 አስከሬኖችን ለማውጣት የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ካገኘ በኋላ ቁፋሮው ተጀምሯል። ሆኖም ከተገመተው በላይ በርካታ አስከሬኖች ተገኝተዋል።

የመንግስት ፓቶሎጂስት ሪቻርድ ንጆሮጌ እንደገለጹት፣ አስከሬኖቹ በጆንያዎች ተጠቅጥቀው የተገኙ ሲሆን ሁኔታው “እጅግ ያልተለመደ” እና “አስደንጋጭ “መሆኑን ገልጸዋል።

የአስከሬን ምርመራ ዛሬ ረቡዕ እንደሚጀመር ይጠበቃል።ሟቾቹን በአስቸኳይ የመለየት እና ለሞታቸው ምክንያት የሆነውን ሁኔታ የማጣራት ስራ እንዲከናወን ጥሪዎች እየቀረቡ ነው።

የምርመራ ሂደቱ በከባድ ዝናብ ምክንያት ለተወሰነ ጊዜ ተቋርጦ የነበረ ቢሆንም፣ አሁን ላይ ግን በከፍተኛ ጥንቃቄ እየተከናወነ ይገኛል።

ይህ ክስተት ከጥቂት አመታት በፊት በኬንያ ከተከሰተው እና በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በረሃብ እንዲሞቱ ካደረገው የሻካሆላ የሃይማኖት ቡድን ጋር ተመሳሳይነት ይኑረው አይኑረው በምርመራው የሚታወቅ ይሆናል ያለው ቢቢሲ ነው።

መጋቢት 16 /2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *