ከ1994 እስከ 1999 ዓ.ም ሀገሪቱን በፕሬዝዳንትነት ያገለገሉት የቀድሞው ወታደር የ84 ዓመቱ ሊያሚን ዘሩዋል ማረፋቸውን ተከትሎ፤ አልጄሪያ ከትናንት ጀምሮ የሦስት ቀናት ብሔራዊ ሐዘን አውጃለች።
ሐምሌ 3 ቀን 1941 በምስራቃዊቷ ባትና ከተማ የተወለዱት ዘሩዋል፤ ከፈረንሳይ ቅኝ አገዛዝ ነፃ ለመውጣት በተዋጋው የአልጄሪያ ብሔራዊ ነፃ አውጪ ጦር ውስጥ አገልግለዋል።
በወቅቱ በነበረው የእርስ በርስ ጦርነት ወቅት የሽግግር አስተዳደርን የመሩት ዘሩዋል፤በ1995 ዓ.ም የሀገሪቱን የመጀመሪያ ባለብዙ ፓርቲ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በማዘጋጀት በከፍተኛ የድምፅ ልዩነት አሸንፈው ነበር።
ይሁን እንጂ በ1998 ዓ.ም ያልተጠበቀ ውሳኔ በማሳለፍ የአምስት ዓመት የሥልጣን ዘመናቸውን ያሳጠሩ ሲሆን፤ ይህም አብደላዚዝ ቡተፍሊካ ተተክተው ሀገሪቱን ለ20 ዓመታት እንዲመሩ መንገድ ከፍቷል።
ዘሩዋል በጡረታ ዘመናቸውም የተከበሩ ሰው ነበሩ።
የአልጄሪያ ፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት ባጋጠማቸው ጽኑ ሕመም ምክንያት በአልጀርስ በሚገኝ ወታደራዊ ሆስፒታል ውስጥ ማረፋቸውን ገልጾ፤ በሀገሪቱ በሙሉ ሰንደቅ ዓላማ ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ አዟል፡፡
እስከዳር ግርማ
መጋቢት 21/2018 ዓ.ም
