በጀነራል ታደሰ ወረደ የሚመራዉ ጊዜያዊ አስተዳደር የስራ ዘመን መጋቢት 30 / 2018 አ.ም ላይ የሚያበቃ ይሆናል።
ይህንን ተከትሎ ባሳለፍነዉ አርብ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጠዉ ኮምሽኑ የጊዜያዊ አሰተዳደሩ የስልጣን ዘመን ማብቃት ኮምሽኑ በቀጣይ በክልሉ ለሚያደርጋቸዉ ስራዎች እንቅፋት ይሆናል ወይ? የሚል ጥያቄ ቀርቧል።
ዋና ኮምሽነር መስፍን አርአያ አስተዳደሩ መጋቢት 30 ያበቃል ማለት የትግራይ ጉዳይ መጨረሻ ነዉ ማለት አይደለም ” ብለዋል።
የክልሉ አስተዳደር ምክክሩን ለማድረግ የቻለዉን ሞክሯል ያሉት ኮምሽነሩ በር ዘግቶብናል ብለን አናስብም ሲሉም አክለዋል።
ሌላኛው ኮምሽን መላኩ ወ/ማርያም የሀገራዊ ምክክሩ ጉዳይ ከአንድ ሰዉ የሰራ ዘመን ጋር የሚያያዝ አለመሆኑን በመግለፅ ስራዉን የሚያስተጓጉልም አይደለም በማለት ምላሽ ሰጥተዋል።
የትግራይ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ እና የተሳታፊዎች ልየታ በመጪዉ መጋቢት 23- 25 በአዲስ አበባ የሚካሄደው ይሆናል።
በሂደቱ ከ4 መቶ በላይ በሚደረገዉ በዚህ ሂደት ይገኛሉ ተብሎም ተጠብቋል።
ቁምነገር አየለ
መጋቢት 21/2018 ዓ.ም
