ኢራን በሆርሙዝ የባህር መስመር ላይ የነበራትን ጫና ለማቆም ፍላጎት አሳይታለች ተባለ

ኢራን ስልታዊ በሆነውና ለዓለም የነዳጅ ንግድ ወሳኝ በሆነው የሆርሙዝ የባህር መስመር ላይ የነበራትን ጥብቅ ቁጥጥር እና ጫና ለማቆም ሃሳብ ማቅረቧ ተሰማ።

አሶሺየትድ ፕሬስ የክልሉን የደህንነት ባለስልጣናት ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው፤ቴህራን በባህር መስመሩ ላይ የሚስተዋለውን ውጥረት ለማርገብ ዝግጁ መሆኗን ገልጻለች።

ይሁን እንጂ ይህ የኢራን የሰላም ጥሪ አወዛጋቢ የሆነውን የኒውክሌር መርሃ ግብሯን የማይመለከትና ከኒውክሌር ድርድሩ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የሌለው መሆኑ ተመላክቷል።

ኢራን ይህን ሃሳብ ያቀረበችው ከኒውክሌር መርሃ ግብሯ ጋር በተያያዘ ከምዕራባውያን አገራት ጋር የገባችበት ውጥረት በቆመበት ሁኔታ ላይ ሆኖ ነው።

የሆርሙዝ የባህር መስመር በዓለም ላይ ካለው የነዳጅ ምርት ውስጥ ሲሶው የሚያልፍበት ወሳኝ መተላለፊያ ሲሆን፤ ኢራን መስመሩን ለመዝጋት በምታደርገው ዛቻ የዓለምን የነዳጅ ገበያ ሲያናውጥ መቆየቱ ይታወሳል።

እስካሁን በጉዳዩ ላይ ከኢራን መንግስት በኩል በይፋ የተሰጠ መግለጫ የለም።

ልዑል ወልዴ

ሚያዚያ 19/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *