የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሩሲያ ገቡ

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በቴህራን እና በዋሽንግተን መካከል ያለው የሰላም ጥረት እርግጠኛ ባልሆነ ሁኔታ ላይ ባለበት ወቅት ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ሩሲያ ገብተዋል።

ሚኒስትሩ ወደ ሞስኮ ያመሩት፣ ቀደም ሲል በፓኪስታን ሊካሄድ የታቀደው ውይይት መክሸፉን ተከትሎ እንደሆነ ተገልጿል።

በተለያዩ የጎረቤት ሀገራት በኩል ሰፊ የዲፕሎማሲ ጥረቶች ሲደረጉ ቢቆዩም፣ በኢራን እና በአሜሪካ መካከል ያለው የሰላም ድርድር አሁንም በአሳሳቢ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ተመልክቷል።

ሚኒስትሩ በሩሲያ ቆይታቸው ከከፍተኛ የሀገሪቱ ባለስልጣናት ጋር በሁለትዮሽ እና በቀጣናዊ የጸጥታ ጉዳዮች ላይ እንደሚመክሩ ይጠበቃል ሲል አል አራቢያ ዘግቧል ።

ልዑል ወልዴ

ሚያዚያ 19/2019 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *