የአገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ዕቅድ ለመደገፍ የሚያግዝ ነዉ የተባለ በዓመት 1.1በመቶ ዝቅተኛ ወለድ የሚታሰብበት የብድር ስምምነት ፀደቀ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 17ኛ መደበኛ ስብሰባው አካሂዷል።

በዚህም በኢትዮጵያ መንግስትና በፈረንሳይ የልማት ኤጀንሲ መካከል የተፈረመውን የ80 ሚሊየን ዩሮ የብድር ስምምነት ረቂቅ አዋጅ መርምሮ አጽድቋል።

ይህ የብድር ስምምነት በዓመት 1.1በመቶ ዝቅተኛ ወለድ የሚታሰብበት ነዉ የተባለ ሲሆን፤0.5 በመቶ የአገልግሎት ክፍያ የሚፈጸምበት እንደሆነ ተነግሯል።

ዛሬ የፀደቀዉ ይህ የብድር ስምምነት የ5 ዓመት የችሮታ ጊዜን ጨምሮ በ15 ዓመታት ውስጥ ተከፍሎ የሚጠናቀቅ ነዉ ተብሏል።

ብድሩ በቀጥታ ወደ መንግሥት ግምጃ ቤት የሚፈስ ነዉ የተባለ ሲሆን፤ ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ ዕድገትን ለማረጋገጥና የመንግሥትን የበጀት አቅም ለማጠናከር ታስቦ የቀረበ ስለመሆኑ ነዉ የተነገረዉ።

ከዚህ በተጨማሪ ምክር ቤቱ በኢትዮጵያ መንግስት እና በአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ ማህበር መካከል የተፈረመውን የ110 ሚሊዮን ዩሮ የብድር ስምምነት አዋጅ መርምሮ ማፅደቁ ታወቋል።

ይህ ብድር በ25 ዓመታት ውስጥ ተከፍሎ የሚጠናቀቅ ተብሏል።

በአውሮፓ ህብረትና ከግብርና ልማት ፈንድ የተገኘው የእርዳታ ድጋፍ የመልሶ መክፈያን ወጪን በመቀነስ ከሀገሪቷ የብድር አስተዳደር ጋር እንዲጠናከር እንዲጣጣም ቀርቧል መባሉን ከምክር ቤቱ የተገኘዉ መረጃ ጠቁሟል።

ሚያዚያ 20/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *