ወንጀል የፈጸሙ ስደተኞችን ማባረር የትራምፕ ሁለተኛው ተወዳጅ ፖሊሲ ሆነ

በአሜሪካ የተካሄደ አዲስ የህዝብ አስተያየት ጥናት፤ ወንጀል የፈጸሙ ህገ-ወጥ ስደተኞችን ከአገር ማባረር የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሁለተኛው ተወዳጅ ፖሊሲ መሆኑን ይፋ አደረገ።

የሃርቫርድ ሲ.ኤ.ፒ.ኤስ በቅርቡ ባወጣው መረጃ መሠረት፣ 73 በመቶ የሚሆኑ አሜሪካውያን መራጮች ወንጀል የፈጸሙ ህገ-ወጥ ስደተኞች በአስቸኳይ ከአገር እንዲባረሩ ድጋፋቸውን ሰጥተዋል።

ይህ ቁጥር ፖሊሲውን ከትራምፕ ዕቅዶች መካከል በሁለተኛ ደረጃ ተወዳጅ እንዲሆን አድርጎታል።

በጥናቱ መሠረት፣ ከመድኃኒት ዋጋ ቅናሽ ቀጥሎ ከፍተኛ ድጋፍ ያገኘው ይህ የኢሚግሬሽን ፖሊሲ፤ አብዛኛው አሜሪካዊ በድንበር ቁጥጥርና በደህንነት ረገድ ጥብቅ እርምጃ እንዲወሰድ እንደሚፈልግ አመላካች ሆኗል።

በተጨማሪም ጥናቱ ካመላከታቸው ነጥቦች መካከል፤83 በመቶ ድጋፍ ያገኘው የመድኃኒት ዋጋን መቀነስ ቀዳሚው ተወዳጅ ፖሊሲ ሆኗል።

67 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ የክልል ባለስልጣናት ወንጀል የፈጸሙ ስደተኞችን አሳልፎ ለመስጠት ከፌዴራል ተቋማት ጋር እንዲተባበሩ ፍላጎታቸውን ገልጸዋል።

በሌላ በኩል፣ 58 በመቶ የሚሆኑት መራጮች የዴሞክራት ፓርቲ “ክፍት ድንበር” እንዲኖር ይፈልጋል የሚል እምነት እንዳላቸው በጥናቱ ተመልክቷል።

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ወደ ስልጣን ከተመለሱ በኋላ በድንበር አካባቢ ጥብቅ ቁጥጥር ለማድረግና መጠነ ሰፊ የማባረር እርምጃዎችን ለመውሰድ ቃል መግባታቸው የሚታወስ ሲሆን፣ ይህ የህዝብ አስተያየት ውጤትም ለፕሬዝዳንቱ ዕቅድ ትልቅ ግብዓት እንደሚሆን ተነግሯል።

ምንጭ :-ዋሽንግተን ፓስት

ልዑል ወልዴ

ሚያዝያ 30/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *