የኢትዮጵያ የምግብና የመድኃኒት ባለሥልጣን የህክምና ሙከራ (Clinical Trial) አሠራርን ወደ ዲጂታል ሥርዓት የሚያሸጋግር አዲስ የኦንላይን ሲስተም በይፋ አስጀምሯል::
በማስጀመሪያ መድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ፍሬይህወት አበበ አዲሱ የዲጂታል ሥርዓት የህክምና ሙከራ ፍቃድ አሰጣጥን ዘመናዊ ከማድረጉም በላይ ግልጽነትን ለማስፈንና የሀብት ብክነትን ለመቀነስ ትልቅ አስተዋፅኦ ይኖረዋል ብለዋል::
የጤና ሚኒስቴር የምርምርና የቁጥጥር ሥርዓቱን የሚያጠናክሩ ፖሊሲዎችን ለመደገፍ ቁርጠኛ ነው ሲሉም አክለዋል::
የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሄራን ገርባ በበኩላቸው፤ ተቋሙ የቁጥጥር ሥርዓቱን ዓለም አቀፍ ደረጃ ለማድረስ ባደረገው ጥረት የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) Maturity ደረጃ 3 (ML3) ማግኘት መቻሉን አስታውሰዋል::
ባለስልጣኑ በቀጣይ የዓለም ጤና ድርጅትን ML4 ደረጃ ላይ ለመድረስና ኢትዮጵያን በአፍሪካ ውስጥ ጥራት ያላቸው የሕክምና ሙከራዎች ተመራጭ መዳረሻ ለማድረግ እንደሚሠራ አስታውቀዋል።
ለዚህ የኦንላይን ሥርዓት መዘርጋት የፋይናንስ ድጋፍ ላደረጉት የጌትስ ፋውንዴሽን እና የዓለም ባንክ ምስጋና አቅርበዋል።
አዲስአለም አበበ
ግንቦት 13/2018 ዓ.ም
