ከደቡብ አፍሪካ ወደ እንዲመለሱ የተደረጉ የመጀመሪያዎቹ የጋና ዜጎች አገራቸዉ ገቡ

በደቡብ አፍሪካ በተቀሰቀሰው የጸረ-ስደተኞች ተቃውሞ ምክንያት ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ የተደረጉ ወደ 300 የሚጠጉ የመጀመሪያዎቹ የጋና ዜጎች አክራ ገብተዋል።

በደቡብ አፍሪካ ደህንነታቸው አስተማማኝ እንዳልሆነ የገለጹ ወደ 800 የሚጠጉ ጋናውያን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ በከፍተኛ ኮሚሽኑ ዘንድ ተመዝግበዋል።

የጋና መንግስት ይህንን የዜጎች ስምሪት ያዘጋጀው ህጋዊና ህገ-ወጥ የውጭ ሀገር ዜጎችን ኢላማ ባደረገው የተቃውሞና የጥቃት ማዕበል ሳቢያ ነው።

የአህጉሪቱ በኢንዱስትሪ የበለጸገች ሀገር የሆነችው ደቡብ አፍሪካ፤ ለረጅም ጊዜ ለህጋዊም ሆነ ለህገ-ወጥ አፍሪካውያን ሰራተኞች ዋነኛ መዳረሻ ሆና ቆይታለች።

ይሁን እንጂ ከ30 በመቶ በላይ በሆነ የሥራ አጥነት መጠን የተጠመደችው ሀገሪቱ፤ ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ የታየውን አዲስ ግጭት ጨምሮ ተደጋጋሚ የውጭ ዜጎች ጥላቻ ተቃውሞዎችን አስተናግዳለች።

የደቡብ አፍሪካ የኢሚግሬሽን ባለስልጣናት እንደገለጹት፤ ህጻናትን ጨምሮ ወደ ሀገራቸው ከተመለሱት 300 ሰዎች መካከል 10ሩ ብቻ በሀገሪቱ በህጋዊ መንገድ ይኖሩ የነበሩ ሲሆን፤ “አብዛኞቹ” ግን የቪዛ ጊዜያቸው ያለፈባቸው ናቸው።

እስከዳር ግርማ

ግንቦት 20/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *