አንድ የፔንስልቬንያ ነዋሪ ባለቤቱ የፍቺ ጥያቄ በማቅረቧ ስለተናደደ፣ ሚስቱና ሁለት ሴት ልጆቹ በቤት ውስጥ እንዳሉ በኤክስካቫተር ቤቱን አፍርሷል ።
የ48 ዓመቱ ኤሪክ ፒየርውዛ፣ ባለቤቱ ትዳራቸው ማብቃቱን ስትነግረው ሌሊቱን ሙሉ ሲጠጣ አድሮ “ሁሉም ነገር ካለቀ ቤቱን አፈርሰዋለሁ” ብሎ በመዛት የቤቱን የጀርባ ክፍል ማፍረስ መጀመሩ ተነግራል።
ቤቱ በሚፈርስበት ወቅትም ባለቤቱ ለ911 ድንገተኛ አደጋ ጥሪ ያደረገች ሲሆን፣ የማፍረሱ ድምጽም በስልኩ ውስጥ ይሰማ ነበር ተብሏል።
እንደ እድል ሆኖም በቤተሰቡ ላይ ምንም ዓይነት የአካል ጉዳት አልደረሰም።
መርማሪዎች እንደገለጹት፣ ምንም እንኳን ጉዳቱ መጀመሪያ ላይ ቀላል ቢመስልም የቤቱ መዋቅር በመናጋቱ ለደህንነት ሲባል ሙሉ በሙሉ መፍረስ አለበት።
ኤሪክ ፒየርውዛ ድርጊቱን ከፈጸመ በኋላ ወደ ከተማ ቢሸሽም በፖሊስ ቁጥጥር ውሎ አሁን ላይ አደጋ ማድረስ እና ሰዎችን ለአደጋ ማጋለጥን ጨምሮ በበርካታ ወንጀሎች መከሰሱን ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል።
ሐመረ ፍሬው
ግንቦት 25/2018 ዓ.ም
