ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የእንጦጦ-ቀጨኔ የወንዝ ዳርቻ ፕሮጀክትን በይፋ መረቁ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ማለዳ፣ከእንጦጦ እስከ ቀጨኔ መድኃኔዓለም ያለውንና 22.25 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነውን የመልሶ ማልማት እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት በይፋ አገልግሎት አስጀምረዋል።

“ይህ ተነሳሽነት፤ የተራቆቱ አካባቢዎችን በዘመናዊ የአፈር ጥበቃ እና በወንዝ ማጣራት ወደ አረንጓዴ ስፍራዎች በመቀየር፣ የፍራፍሬ ፓርኮችን ከእግር ጉዞ እና ከብስክሌት መንገዶች ጋር በማቀናጀት መዲናዋ አዲስ አበባን ይበልጥ የሚያድስ ነው” ሲሉ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህ ፕሮጀክት፣ የሀገራዊ ዕድገት፣ የአካባቢ ጥበቃ እና የከተማ ዕድሳት በተግባር የታየበት መሆኑን ገልጸዋል።

ግንቦት 25/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *