የቀድሞ የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር የሊባኖስን የተኩስ አቁም ተችተዋል።

የቀድሞ የእስራኤል መከላከያ ሚንስትር እና የእስራኤል ቤይቴኑ ፓርቲ መሪ አቪግዶር ሊበርማን፤ የሊባኖስን የተኩስ አቁም ስምምነት ሄዝቦላህ እንደገና እንዲሰባሰብ እና ኃይሉን መልሶ ለመገንባት ጊዜ ይሰጣል ሲሉ ተችተዋል።

በኤክስ ገፃቸዉ ላይ ባሰፈሩት መልዕክትም ሊበርማን ስምምነቱ ወደ ጥቅምት 7 ወዳደረሰን ጽንሰ-ሐሳብ መመለስ” ነው ብለዋል።

ሊበርማን አክለውም ጦርነቱ በቆራጥነት መጠናቀቅ አለበት ብለዋል ሲል አልጀዚራ ዘግቧል።

ሊዲያ ደሳለኝ

ግንቦት 27/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *