የቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ በሰሜን ኮሪያ ይፋዊ ጉብኝት እያደረጉ ነው

የቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ ከ2019 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በሰሜን ኮሪያ የሚያደርጉትን ታሪካዊ ጉብኝት ለመጀመር ፒዮንግያንግ ገብተዋል።

ፕሬዝዳንቱ ፒዮንግያንግ ሲደርሱ የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን እና ባለቤታቸው ሪ ሶል ጁ በአውሮፕላን ማረፊያው በመገኘት ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በቀይ ምንጣፍ እና በወታደራዊ ሰልፍ የታጀበው አቀባበል፣ የሁለቱን ሀገራት “የማይበገር ወዳጅነት” የሚያወድሱ መፈክሮች የታዩበትነበር።

ቻይና በዓለም አቀፍ ማዕቀቦች ለተዳከመችው ሰሜን ኮሪያ ዋነኛ የንግድ አጋር እና የዲፕሎማሲ ደጋፊ መሆኗ ይታወቃል።

ይህ ጉብኝት የተከናወነው በሰሜን ኮሪያ እና በአሜሪካ መካከል ያለው የኒውክሌር ድርድር ባለመቀጠሉ ውጥረት በነገሰበት ወቅት ነው።

ፕሬዝዳንት ሺ ከዚህ ቀደም ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና ከሩሲያው ቭላድሚር ፑቲን ጋር በቤጂንግ መወያየታቸው ይታወሳል።

ምንም እንኳን ዋይት ሃውስ ቻይና እና አሜሪካ ሰሜን ኮሪያን ከኒውክሌር መሳሪያ ነፃ የማድረግ የጋራ ግብ አላቸው ቢልም፣ የኪም ጆንግ ኡን እህት ግን የሀገሪቱ የኒውክሌር መርሃ ግብር “ሊመለሱበት የማይችሉት ቀይ መስመር” መሆኑን ገልጸዋል።

በሌላ በኩልየደቡብ ኮሪያው ፕሬዝዳንት ሊ ጄምዩንግ ሰሜን ኮሪያ አሁንም የኒውክሌር ግብአቶችን እያመረተች መሆኑን በመጥቀስ፣ የዲፕሎማሲ ጥረቱ ሊቀጥል እንደሚገባ አሳስበዋል።

ለዓለም አሰፋ

ሰኔ 01/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *