የ 8 መቶ 16 የምርጫ ክልሎች ዉጤት ወደ ማዕከል መግባቱ ተገለፀ

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ትናንት ማምሻዉን በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ የ24 የምርጫ ክልሎችን ዉጤት በመግለፅ ማፅደቁን አስታዉቋል።

የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላተወርቅ ሀይሉ ወደ ማዕከል የመጡ እና የደረሱ ዉጤቶችን ቦርዱ ማፅደቅ መጀመሩን ትላንት ማምሻውን በሰጡት በመግለጫዉ ተናግረዋል።

ሰብሳቢዋ እንደተናገሩት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የድምፅ ማዳመር ዉጤት በመጠናቀቅ 3 መቶ 53 የምርጫ ክልሎች ዉጤቶች ወደ ማዕከል ገብተዋል።

ከዚህ ዉጪ ካሉት የክልል ምክር ቤት መቀመጫዎች የ4 መቶ 63 የምርጫ ክልሎች ዉጤት ወደ ማዕከሉ መግባት መቻሉን ሰብሳቢዋ በትናንትናው መግለጫቸዉ ተናግረዋል።

ቀሪ የምርጫ ክልሎች ዉጤት በጉዞ ላይ እንደሚገኙ እና ቀሪ ዉጤት ያለጠፉ ሁለት የምርጫ ክልሎች መኖራቸዉንም አያይዘው ገልፀዋል።

ፓርቲዎች እያቀረቧቸዉ ያሉት የምርጫ አፈፃፀም ጥሰት መኖሩን በመግለፅ የዳግም ምርጫ ይደረግ የሚል ጥያቄን ተከትሎ ምላሽ የሰጡት ሰብሳቢዋ ቦርዱ ያቋቋመው የህግ ባለሙያዎች ጉባኤዉ በማስረጃ የተደረገፈ ማጣራት እና ምስክሮችን የማድመጥ ስራ ላይ መሆኑን ገልፀዋል።

ጉባኤዉ የምርጫ አፈጻጸም ጥሰት አለ ብሎ ካረጋገጠ ለቦርዱ ዉሳኔ የሚልክ መሆኑን የገለፁት ሰብሳቢዋ ቦርዱ ድምፅ በመሠረዝ የዳግም ምርጫ የሚያደርግበት ሂደት አለ ብለዋል።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የደረሱ ዉጤቶችን ዉጤቶች ይፋ እንደሚያደርግ ተገልፆል።

ቁምነገር አየለ

ሰኔ 03/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *