ለበጀት ጉድለት መሸፈኛ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ የሚወሰደው ብድር ሙሉ በሙሉ መቆሙን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ገልጸዋል፡፡
ሚኒስትሩ ይህንን የገለጹት የ2019 በጀት ዓመት ዓመታዊ የበጀት መግለጫን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡበት ወቅት ነው፡፡
የገንዘብ ፖሊሲ ማዕቀፉን ዘመናዊ በማድረግና የወለድ ምጣኔን በገበያ እንዲመራ በመደረጉ የፋይናንስ ዘርፉን ጤናማነትና ዘላቂነት ማረጋገጥ መቻሉን ተናግረዋል፡፡
አቶ አህመድ ሽዴ አክለውም የብሔራዊ ባንክ የፖሊሲ ወለድ ምጣኔ ተግባራዊ በመደረጉ ዘመናዊ የገንዘብ ፖሊሲውን የሚያጠናክሩ በርካታ ለውጦች እየተመዘገቡ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
ለበጀት ጉድለት ከብሔራዊ ባንክ ባለመወሰዱ የዋጋ ንረት ወደ ነጠላ አሃዝ መውረዱንም ክብር ሚኒስትሩ ጨምረው አብራርተዋል፡፡
ብሔራዊ ባንክ የዘረጋውን ዘመናዊ የገንዘብ ፖሊሲ ለማስጠበቅ የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ክቡር ሚኒስትሩ ጨምረው ገልጸዋል፡፡
የባንክ አገልግሎት ደረጃ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መሆኑንም አቶ አህመድ ሽዴ ተናግረዋል፡፡
ሰኔ 04/2018 ዓ.ም
