በካሊፎርኒያ የአሜሪካ አየር ኃይል ቢ-52 ቦምብ ጣይ አውሮፕላን ተከስክሶ የስምንት ሰዎች ሕይወት አለፈ

በደቡብ ካሊፎርኒያ ከሚገኘው የኤድዋርድስ አየር ኃይል ማዕከል ለመነሳት በሞከረበት ቅጽበት በተከሰከሰው የዩናይትድ ስቴትስ አየር ኃይል ቢ-52 ቦምብ ጣይ አውሮፕላን አደጋ፥ ሁለት የቦይንግ ኩባንያ ሠራተኞችን ጨምሮ የስምንት ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተረጋግጧል።

አደጋው የተከሰተው ሰኞ ዕለት በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከቀኑ 11:20 ላይ አውሮፕላኑ በተለመደው የሙከራ ተልዕኮ ላይ በነበረበት ወቅት ነው።

የአውሮፕላኑ መከስከስ ለብዙ ማይሎች ሊታይ የሚችል ግዙፍ የጥቁር ጭስ ደመና በአየር ላይ አስከትሏል።

የአየር ኃይል ማዕከሉ ቀደም ሲል ባወጣው መግለጫ፥ በመጀመሪያ አደጋው ‹‹ማንም ሊተርፍበት የማይችል›› እንደነበረ የሚያሳይ መሆኑን በመግለጽ፤ የሟቾች የቅርብ ቤተሰቦች መርዶ እየተነገራቸው አሳውቋል፡፡

ይህ ከተጠናቀቀ ከ24 ሰዓታት በኋላ ስማቸው ይፋ ይደረጋል ተብሏል፡፡

አደጋው ሙሉ በሙሉ በኤድዋርድስ አየር ኃይል ማዕከል የማረፊያ መስመር ክልል ውስጥ የተገደበ እንደነበር የተገለፀ ሲሆን፤ ማዕከሉ የዕለት ተዕለት ሥራዎቹን ለጊዜው ማገዱን አስታውቀዋል።

ቢ-52 አውሮፕላኑ የማዕከሉን የራዳር ዘመናዊነት ፕሮግራም እየደገፈ እንደነበረና ለመነሳት በሞከረበት ቅጽበት ተከስክሶ በእሳት መያያዙም ታውቋል።

ሀና ሰይፉ

ሰኔ 09/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *