በደቡብ አፍሪካ በግንቦት ወር የተመዘገበው የሸማቾች የዋጋ ንረት መጠን 4.5 በመቶ መድረሱ ታወቀ።
ምንም እንኳን መጠኑ በዓመት አሀዝ ካለፈው ወር የ 4 በመቶ ጭማሪ ቢያሳይም፣ የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ቀደም ብለው ከገመቱት የ 4.7 በመቶ ጭማሪ በታች መሆኑ ተገልጿል።
የሀገሪቱ የስታቲስቲክስ ተቋም ባወጣው መረጃ መሠረት፣ የወርሃዊ የዋጋ ንረት ዕድገቱ ካለፈው ወር ከነበረበት 0.7 በመቶ ወደ 1.1 በመቶ ከፍ ብሏል።
ለዚህ የዋጋ ግሽበት ዋነኛ መንስኤዎች በነዳጅ እና በምግብ ምርቶች ላይ የታየው የዋጋ ጭማሪ እንዲሁም በዓለም አቀፍ የኃይል ገበያ ላይ የተከሰቱት መዋዠቆች መሆናቸውን ባለሙያዎች አመልክተዋል።
የደቡብ አፍሪካ ማዕከላዊ ባንክ የዋጋ ንረትን በ3 በመቶ አካባቢ ለመገደብ ግብ ጥሎ እየሰራ ይገኛል። ባንኩ ይህንን ግሽበት ለመቆጣጠር በወሰደው እርምጃ፣ በግንቦት ወር መጨረሻ ላይ ባካሄደው የገንዘብ ፖሊሲ ስብሰባ የብድር ወለድ መጠኑን ከፍ አድርጓል።
ይህ የባንኩ ውሳኔ ባለፉት ሦስት ዓመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የተደረገ የወለድ መጠን ጭማሪ መሆኑ ሮይተርስ በዘገባው ጠቅሷል፡፡
ትዕግስት ግርማ
ሰኔ 10/2018 ዓ.ም
በደቡብ አፍሪካ የታየው የዋጋ ንረት የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ከገመቱት በታች መሆኑ ተገለጠ
