ትራምፕ በዩክሬን ሰላም እንዲወርድ ግፊት እንደሚያደርጉ ተናገሩ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በፈረንሳይ በተካሄደው የጂ7 መሪዎች ጉባኤ ላይ ከፕሬዘዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ጋር “በጣም ጥሩ” ውይይት ማድረጋቸውን ተከትሎ ሩሲያ ከዩክሬን ጋር የሰላም ስምምነት ማድረግ እንዳለባትና እርሳቸውም ጦርነቱን ለማቆም የሚችሉትን ሁሉ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።

ትራምፕ በጦርነቱ በርካታ ወጣቶች እያለቁ መሆኑን በመጥቀስ “እኔ ስምንት ጦርነቶችን አስቆሜያለሁ ይህኛው ግን ለመፍታት በጣም ቀላሉ ይሆናል ብዬ ያሰብኩት ነበር” ብለዋል።

ይሁን እንጂ ስምንት ጦርነቶችን አስቆሜያለሁ ማለታቸው በሰፊው አከራካሪ ሆኗል።

ዘለንስኪ ከጂ7 መሪዎች፣ ከትራምፕ እና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ጋር ከተወያዩ በኋላ በኤክስ  ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት፥ ዋናው ትኩረት የዩክሬንን የአየር መከላከያ ማጠናከርና ዲፕሎማሲውን ማራመድ እንደሆነ ገልጸዋል።

ከጂ7 መሪዎች ጠቃሚ የሆኑ የቃል ኪዳን ድጋፎችን ተጨማሪ ሚሳኤሎች፣ የማምረቻ ፈቃድ እና የክረምት ድጋፍ ማግኘታቸውን የገለጹት ዘለንስኪ፥ አሜሪካ ለዚህ ሁሉ ዋስትና ለመስጠት ዝግጁ መሆኗን አክለዉ ተናግረዋል ።

የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኡርሱላ ፎን ደር ላየንም በበኩላቸው የጦርነቱ አቅጣጫ ወደ ዩክሬን እየተቀየረ መሆኑንና የሩሲያ ድካም በግልጽ እየታየ በመሆኑ ድጋፍን እጥፍ ለማድረግ ጊዜው አሁን እንደሆነ ተናግረዋል።

ትኩረትበሆርሙዝየባህርወሽመጥላይ የጂ7 መሪዎች ከአሜሪካ እና ኢራን የሰላም ስምምነት በተጨማሪ የሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ በፍጥነት እንዲከፈት እና አማራጭ የኢነርጂ መስመሮችን በመለየት ላይ ያተኮረ ውይይት አድርገዋል።

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ዋነኛው ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ጠንካራ ስምምነት መፈረሙን ማረጋገጥ እንደሆነና ፈረንሳይና ሌሎች ምዕራባውያን አጋሮች ወሽመጡ በሰላም እንዲከፈት በፍጥነት ለመርዳት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ትራምፕ የሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ አርብ ዕለት “ሙሉ በሙሉ ክፍት” እንደሚሆን እና ይፋዊው ስምምነት በጄኔቫ እንደሚፈረም ተናግረዋል።

በዲጂታል መልኩ የተፈረመው ይህ ስምምነት፥ የኢራንን የበለጸገ ዩራኒየም እና ማዕቀቦችን ማንሳትን የሚያካትቱ ውስብስብ ድርድሮች የሚካሄዱበት የ60 ቀናት ጊዜ የሚከፍት ሲሆን፤ ትራምፕ ሁለተኛው የውይይት ምዕራፍ ቀላል እንደሚሆን ገልጸዋል።

ሳራ ዮሐንስ

ሰኔ 10/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *