መንግሥትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ለአረጋውያን ጥበቃ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ

የኢትዮጵያ አረጋውያንና ጡረተኞች ማኅበር በአረጋውያን ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን እና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ለመግታት ወጥነት ያለው አሠራር እንዲዘረጋ ጠየቀ።

ይህ የተገለጸዉ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከኸልፕ ኤጅ ጋር በመተባበር ዛሬ ሰኔ 11 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም አቀፉ አረጋውያን ጥቃት መከላከል ቀንን ምክንያት በማድረግ ባዘጋጁት የውይይት መድረክ ነው።

የኢትዮጵያ አረጋውያንና ጡረተኞች ማኅበር ምክትል ቦርድ ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ክፍሉ እንደገለጹት፤ አረጋውያን መብታቸው ተከብሮ መኖር ሲገባቸው በልጆቻቸውና በቅርብ ሰዎቻቸው አማካኝነት ወደ ጎዳና እየተገፉ ነው፡፡

መንግሥት የችግሩን አሳሳቢነት በመረዳት ለአረጋውያን ልዩ ትኩረት መስጠት እንዳለበትም አቶ ጌታቸው አሳስበዋል።

በአረጋውያን ላይ የሚደርሰውን የፆታ ጥቃት እና የሰብዓዊ መብት ጥሰት ለማስቆም ከበዓል ማክበር ባለፈ ዘላቂ ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ እንደሆነ በውይይቱ ተነስቷል።

ሊዲያ ደሳለኝ

ሰኔ 12/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *