የአሜሪካ ኢራን ድርድር በስዊዘርላንድ አበረታች ውጤት ማስመዝገቡ ተገለጸ

በስዊዘርላንድ ለ18 ሰዓታት የተካሄደው የአሜሪካና ኢራን ከፍተኛ ደረጃ ውይይት አበረታች እድገት ማሳየቱን አስታራቂ አገራት ፓኪስታንና ኳታር ገልጸዋል።

ሁለቱ ወገኖች በ60 ቀናት ውስጥ የመጨረሻ ስምምነት ለመድረስ መስማማታቸውም ተነግሯል።

የኢራን ዋና ተደራዳሪዎች ውይይቱን አጠናቀው ወደ ቴህራን ሲመለሱ፤ የቴክኒክ ባለሙያዎች ቡድን በኢስላማባድ መግባቢያ ሰነድ ዙሪያ ድርድሩን እንዲቀጥል በስዊዘርላንድ ቀርቷል።

ከዚህ በፊት የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን ለሄዝቦላህ የምትሰጠውን ድጋፍ በመጥቀስ የወታደራዊ እርምጃ ዛቻ ሲያሰሙ የኢራን ተደራዳሪ መሀመድ ባገር ጋሊባፍ አሜሪካ በንግግሯ ጥንቃቄ እንድታደርግ አስጠንቅቀዋል።

በሌላ በኩል የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ፤ የእስራኤል ጦር በደቡብ ሊባኖስ እስከሚያስፈልገው ድረስ እንደሚቆይ ሲገልጹ፤ ሄዝቦላህ በተኩስ አቁም ስምምነቱ ላይ የሚደረግን ማንኛውንም ጥሰት እንደሚቃወም አስታውቋል::

ትዕግስት ግርማ

ሰኔ 15/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *