እስራኤል በጋዛ፣ በሊባኖስና በሶሪያ የመሬት ቁጥጥሯን አስፋፋች

ባለፉት ሁለት ዓመት ተኩል ውስጥ እስራኤል በጋዛ፣በሊባኖስና በሶሪያ ከ1 ሺህ ካሬ ኪሎ ሜትር በላይ መሬት በወታደራዊ ቁጥጥሯ ስር ማስገባቷ ተዘግቧል።

ይህም በብዙ ዓመታት ውስጥ የታየ ትልቁ የተያዘ መሬት መስፋፋት መሆኑ ተገልጿል።

በተሰበሰበ መረጃ መሠረት እስራኤል በአሁኑ ጊዜ 6መቶ8 ካሬ ኪሎ ሜትር በሊባኖስ፣ 1መቶ94 ካሬ ኪሎ ሜትር በጋዛ 2መቶ35 ካሬ ኪሎ ሜትር በሶሪያ በድምሩ ከ1ሺህ 37 ካሬ ኪሎ ሜትር በላይ መሬት ተቆጣጥራለች።

ይህ ስፋት እስራኤል ከተመሠረተችበት ወቅት ከነበራት ግዛት ከ5 በመቶ በላይ እንደሚሆን ተጠቁሟል።

የመሬት መያዙ በአካባቢዎቹ ላይ ከፍተኛ ሰብዓዊ ተጽዕኖ በማሳደሩ ከ3 ሚሊየን በላይ ሰዎች ከመኖሪያ ቤታቸው እንዲፈናቀሉ ምክንያት ሆኗል ተብሏል።

ትዕግስት ግርማ

ሰኔ 16/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *