ፓኪስታን በምስራቅ አፍጋኒስታን የሚገኙ ታጣቂዎች መደበቂያ ቦታዎች ላይ የአየር እና የምድር ጥቃቶችን መፈጸሟን ገለጸች።
በፓኪስታን ውስጥ ለተፈጸሙት ተከታታይ ገዳይ ጥቃቶች ምላሽ ለመስጠት የተከናወነ ነው በተባለው በዚህ ኦፕሬሽን 29 አሸባሪዎች መገደላቸውን አስታውቃለች።
የማዕከላዊ መረጃ ሚኒስትር እንደገለጹት፤በሶስት የምስራቅ አፍጋኒስታን ግዛቶች በፓክቲያ፣ፓክቲካ እና ኩናር የሚገኙ ሶስት ኢላማዎች በትክክለኛ የዒላማ ምት ወድመዋል ብለዋል።
እነዚህ የአየር ጥቃቶች በፓኪስታን እና አፍጋኒስታን ድንበር ላይ የተካሄዱ የደህንነት መረጃዎችን መሰረት ያደረጉ የምድር ላይ ኦፕሬሽኖችንም ያካተተ ሰፊ ዘመቻ አካል ናቸው።
ይህ ሌሊቱን ሙሉ የተካሄደው ጥቃት የተሰነዘረው ቅዳሜ ዕለት በደቡባዊቷ ካራቺ ከተማ ሶስት የከፊል-ወታደራዊ አባላትን ለገደለው ጥቃት እና በቅርቡ በፓኪስታን የድንበር ግዛቶች ላይ ለተከሰቱት ሁከቶች ምላሽ ለመስጠት ነው።
አሶሺየትድ ፕሬስ የጸጥታ ባለስልጣናትን ጠቅሶ እንደዘገበው፤የፓኪስታን የጸጥታ ኃይሎች እሁድ ዕለት በፓኪስታን እና አፍጋኒስታን ድንበር ላይ የደህንነት መረጃን መሰረት ያደረገ የምድር ላይ ኦፕሬሽን አካሂደዋል።
ሀና ሰይፉ
ሰኔ 22/2018 ዓ.ም
