ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባለፉት አምስት ዓመታት አገራቸውን በታማኝነትና በቁርጠኝነት ላገለገሉ ዜጎች መንግሥት የላቀ ምስጋና እንደሚያቀርብ ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት በ6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 30ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ተገኝተው፣ ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ በሰጡበት ወቅት ነው።
በምክር ቤቱ የነበሩ የተፎካካሪ ፓርቲ አባላትን በተለየ መልኩ ያመሰገኑት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ “ሐሳባችሁን በግልጽ ለመናገር የደፈራችሁ፣ በሰላማዊ መንገድ ለመታገል የሞከራችሁ እና ሐሳባችሁ ምንም ይሁን ምን በግልጽነት ለማቅረብ ጥረት ያደረጋችሁ ሁሉ ጀግኖች ናችሁ” በማለት አጋርነታቸውን ገልጸዋል።
ይሁን እንጂ የትብብር መስኩ በፓርላማ ብቻ ሊወሰን እንደማይገባ ያመለከቱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ ሁሉም ወገኖች ልብና አእምሯቸውን በማስፋት፣ በተለይም በኮሪደር ልማትና መሰል አገራዊ ፕሮጀክቶች ላይ በጋራ እንዲሠሩ ጥሪ አቅርበዋል። አያይዘውም የ27 ዓመታት የልማት ተግባር በአንድ ዓመት ውስጥ እንዲጠናቀቅ ላገዘው ፈጣሪ ምስጋና ይግባው ብለዋል።
የኢትዮጵያ ብልጽግና እስኪረጋገጥ ድረስ በጋራ መቆም እንደሚገባ ያሳሰቡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የመንግሥት ኃላፊዎች፣ ፖለቲከኞች፣ የሃይማኖት አባቶችና የአገር ሽማግሌዎችን አቅም በመጠቀም በእስር ላይ ያሉትን ለመፍታት፣ በውጭና በጫካ ያሉትን ደግሞ ወደ ሰላማዊ መንገድ ለመመለስ ሰፊ ልብና ይቅር ባይነት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል። ይህንን የምናደርገውና የምንተዋወው ግን “ስለ ኢትዮጵያ ስንል ነው” ሲሉ ንግግራቸውን አጠቃለዋል።
ሰኔ 30/2018 ዓ.ም
“ሐሳባችሁን በግልጽ ለመናገር የደፈራችሁ፣ በሰላማዊ መንገድ ለመታገል የሞከራችሁ እና ሐሳባችሁ ምንም ይሁን ምን በግልጽነት ለማቅረብ ጥረት ያደረጋችሁ ሁሉ ጀግኖች ናችሁ” አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
