በትምህርት ሚኒስቴር ሥር የሚታየው የአመራርና የፖሊሲ ውድቀት ለሀገሪቱ የትውልድ ቀውስ ዋነኛ ምክንያት መሆኑ ተገለጸ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ እንደገለጹት፣ በትምህርት ሚኒስቴር ሥር የሚስተዋለው አጠቃላይ የአፈፃፀም መውደቅ እና የፖሊሲ ቀውስ ለሀገሪቱ ስትራቴጂካዊ ስጋት እየሆነ መጥቷል።

ባለፉት ዓመታት በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የተዘረጉት መዋቅሮችና የወጡት መመሪያዎች በተግባር ፍሬ ማፍራት ባለመቻላቸው፣ የትምህርት ሥርዓቱ በጥራትም ሆነ በተደራሽነት ወደ ከፋ ደረጃ እንዲያሽቆለቁል አድርጎታል።

ዶክተር ደሳለኝ አክለውም፣ ሚኒስቴሩ በሀገሪቱ ካለው አለመረጋጋት ጋር ተያይዞ የመጡትን ተግዳሮቶች በአግባቡ መወጣት ባለመቻሉና ከቀውሱ ጋር የሚመጥን ስትራቴጂ በመንደፍ ረገድ ድክመት በማሳየቱ የትምህርት ዘርፉ መውደቅን አስከትሏል።

ይህ የአመራር መውደቅ ደግሞ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተማሪዎችን መፃኢ ተስፋ አደጋ ላይ ከመጣሉም በላይ፣ ሚኒስቴሩ ለተደቀኑት ችግሮች ተገቢውን አካታችና ዘላቂ መፍትሔ ማቅረብ እንዳልቻለ አመላካች ነው ብለዋል።

በመሆኑም መንግሥት በትምህርት ሚኒስቴር ሥር ያሉትን መዋቅራዊና ፖሊሲ ነክ ውድቀቶች በአስቸኳይ በመገምገም፣ ሥር ነቀል ማሻሻያ እንዲያደርግ በጥብቅ አሳስበዋል።

ልዑል ወልዴ

ሰኔ 30/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *