ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የሕዝቡን ውሳኔ “ባዶ ቼክ” ሲሉ ገለጹ፤ በአግባቡ ካልተያዘ የተቃርኖ እርምጃ ሊከተል እንደሚችል አስጠነቀቁ


 የኢትዮጵያ ሕዝብ መከራና ስጋትን ሳይፈራ የሰጠው ድምፅ መንግሥትን በኃላፊነት የሚያስጠይቅ “ባዶ ቼክ” መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ ይህንን አደራ በአግባቡ ካልተጠቀምንበት ሕዝቡ ጥይት ሳይፈራ እንደመረጠን ሁሉ ጥይት ሳይፈራ የተቃርኖ እርምጃ ሊወስድ እንደሚችል አስጠንቀቀዋል።
 
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት ዛሬ በተካሄደው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት 30ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ነው።
 
ሕዝቡ የከፈለውን መስዋዕትነትና ያሳየውን ጽናት “ትልቅ አደራ” ሲሉ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ “በዚያ ሁሉ መከራና ስጋት ውስጥ ወጥቶ የመረጠን ሕዝብ የሰጠን ድምፅ ዝም ብሎ ወንበር ሳይሆን፣ ከባድ አደራ ነው” ብለዋል።
 
በሕዝቡ በተሰጠው በዚህ “ባዶ ቼክ” ላይ መልካም ስም፣ መልካም ሥራና መልካም ውጤት ማምጣት የመንግሥትና የምክር ቤቱ አባላት የጋራ ኃላፊነት መሆኑን ጠቁመው፤ ውጤታማ መሆን የሚቻለውም በታማኝነትና ሕዝብን በማክበር ማገልገል ሲቻል ብቻ እንደሆነ አሳስበዋል።
 
አያይዘውም መንግሥት ይህንን የሕዝብ አደራ በአግባቡ በመረዳት፣ የዜጎችን ሰላም፣ ልማትና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ለማስከበር በቁርጠኝነት እንደሚሠራ ቃል ገብተዋል።
 
ሰኔ 30/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *