ሩሲያ በኪቭ ላይ ዳግም የሚሳኤል ጥቃት ሰነዘረች

የሩሲያ ባለስልጣናት እንደገለጹት፤ ሩሲያ በዩክሬን መዲና ኪቭ ላይ በሳምንት ውስጥ ለሶስተኛ ጊዜ የባሊስቲክ ሚሳኤል ጥቃት ፈጽማለች።

ይህ ጥቃት የተፈጸመው ዩክሬን ከአሜሪካ የሚቀርብላትን የሚሳኤል መከላከያ በመጠባበቅ ላይ ባለችበት ወቅት ነው።

ጥቃቱ ያጋጠመው በቱርክ አንካራ የኔቶ ጉባኤ እየተካሄደ ባለበት እና የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ጋር ለመወያየት በዝግጅት ላይ ባሉበት ወቅት ነው።

የዩክሬን የአየር መከላከያ ከተተኮሱት 1መቶ69 ድሮኖች ውስጥ ከ80 በመቶ በላይ ማክሸፍ ቢችልም፤አምስቱን የባሊስቲክ ሚሳኤሎች ግን ማክሸፍ እንዳልተቻለ የአየር ኃይል መረጃዎች ያሳያሉ።

በዚሁ በተፈጸመው የሌሊት ጥቃት የአንዲት ሴት ህይወት ሲያልፍ ሁለት ሰዎች ቆስለዋል።

ትራምፕ ከጉባኤው አስቀድሞ ከዘለንስኪ እና ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር መነጋገራቸውን ገልጸው፤ጦርነቱ ‹‹በቅርቡ እልባት ያገኛል››የሚል እምነት እንዳላቸው ተናግረዋል።

ፑቲን በበኩላቸው በሩሲያ ላይ እየደረሱ ያሉ ተግዳሮቶች ቢኖሩም ጦርነታቸውን እንደሚገፉበት አስታውቀዋል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።

እድላዊት ብርሃኑ

ሐምሌ 01/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *