ኢራን አሜሪካ በበርካታ የኢራን ኢላማዎች ላይ ላደረሰችው ጥቃት ምላሽ ለመስጠት በባህሬንና በኩዌት የሚገኙ የአሜሪካ ወታደራዊ ይዞታዎችን ኢላማ እያደረገች መሆኑን አስታውቃለች።
የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ በሰጠው መግለጫ፤ ከ60 በላይ የኢስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ትናንሽ ጀልባዎችን ጨምሮ ከ80 በላይ ኢላማዎችን መምታቱን ገልጿል።
የኢራን የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን እንደዘገቡት ከሆነ ጥቃቱ ባንደር አባስ እና ሲሪክ የተባሉ አካባቢዎችን ያካተተ ሲሆን፤ በጥቃቱም የተወሰኑ ሰዎች በብረት ስብርባሪ መቁሰላቸው ታውቋል።
ይህ እርምጃ የተወሰደው በሆርሙዝ ባህረ ሰላጤ ውስጥ በሦስት የነዳጅ ጫኝ መርከቦች ላይ ከተፈጸመው ጥቃት በኋላ ሲሆን ኢራን ለጥቃቱ በቀጥታ ኃላፊነቱን አልወሰደችም።
ቀደም ሲል የኔቶ ዋና ፀሐፊ ማርክ ሩቴ ኢራን ‹‹መርከቦችን በማጥቃት የተኩስ አቁም ስምምነቱን በግልጽ እየጣሰች ነው›› በማለት በመክሰስ የአሜሪካ ጥቃት ‹‹ፍጹም አስፈላጊ›› ነበር ብለዋል።
በሌላ በኩል የኢራን ፓርላማ አፈ-ጉባኤ መሐመድ ባግኃር ጋሊባፍ አሜሪካ በሆርሙዝ ባህረ ሰላጤ ላይ የተደረጉ የኢራንን ማስተካከያዎች በመጣስ የመግባቢያ ስምምነቱን ያፈረሰችው እራሷ አሜሪካ መሆኗን ተናግረዋል።
ባለፈው ወር ቴህራን እና ዋሽንግተን የተኩስ አቁም ስምምነቱን ለማራዘም እና ግጭቱን ‹‹በሁሉም ግንባሮች›› ለማቆም ያለመ ባለ 14 ገጽ የተግባቦት ስምምነት ተፈራርመው ነበር።
ሀና ሰይፉ
ሐምሌ 01/2018 ዓ.ም
