ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ የ2018 በጀት አፈፃፀም ባወጣዉ ሪፖርት 16 ማደያወችን ማስጠንቀቂያ መስጠቱንና ከመሸጫ ዋጋ በላይ በሚሸጡ ማደያወች ላይም እርምጃዎች መወሰዱን ገልጿል ።
በኢትዮጵያ የነዳጅ ስርጭት እና ግብይት ሂደት ላይ የሚታዩ ህገ-ወጥ ተግባራትን ለመቆጣጠር በተደረገ ክትትል፣ በበርካታ ኩባንያዎች እና የነዳጅ ማደያዎች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃዎች መወሰዳቸው ተገልጿል ።
በህገ-ወጥ የነዳጅ ግብይት ስራ ላይ ተሰማርተው የተገኙ ስምንት የሚሆኑ የነዳጅ ኩባንያዎች እስከ ሶስት ወር የሚደርስ እገዳ ተጥሎባቸዋል።
ከጅቡቲ ነዳጅ ጭነው ሲመጡ መድረሻ ቦታቸውን በመቀየር እና በመቅሸብ ስራ ላይ የተሰማሩ 15 የሚሆኑ ቦቴዎች ላይም እርምጃ ተወስዷል።
መንግስት የነዳጅ እጥረትን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ህገ-ወጥ ትርፍ ለማግኘት የሚሞክሩ አካላትን ለመቆጣጠር የህዝቡ ጥቆማ እና ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን አሳስቧል።
ሊዲያ ደሳለኝ
ሐምሌ 02/2018 ዓ.ም
