አሜሪካ ለዲፕሎማሲ ዕድል ለመስጠት በኢራን ላይ የምታደርገውን ጥቃት አቁማለች ተባለ

በአሁኑ ወቅት በአሜሪካ እና በኢራን መካከል ያለውን ውጥረት ለማርገብ በስተጀርባ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች እየተደረጉ መሆኑን አንድ ባለስልጣን ለሲኤንኤን ገልጸዋል።

ሲኤንኤን የአሜሪካ ባለስልጣናትን ጠቅሶ እንደዘገበው፤በአሜሪካ እና በኢራን ግጭት ውስጥ ያለውን ውጥረት ለማርገብ በአሁኑ ጊዜ በስተጀርባ ዲፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴዎች እየተከናወኑ ነው።

ውጥረቱ እንዳይባባስ እና ዲፕሎማሲው ውጤታማ እንዲሆን አሜሪካ ሆን ብላ ጥቃት በመሰንዘር እና ከዚያም ጥቃቱን በማቆም ላይ እንደምትገኝ አንድ የአሜሪካ ባለስልጣን ተናግረዋል።

በተጨማሪም እንደ መደራደሪያ ለመጠቀም የታለመላቸውን የጥቃት ቦታዎች ዝርዝር ይዛ ትገኛለች።

አስፈላጊ ከሆነ ዛሬ ምሽት ሊሰነዘሩ ለሚችሉ ጥቃቶች ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን በርካታ ባለስልጣናት ቢናገሩም፤በአሁኑ ወቅት ግን ለዲፕሎማሲው ቅድሚያ እየተሰጠ መሆኑ ተገልጿል።

ተጨማሪ የአሜሪካ ጥቃቶች ተፈጽመዋል የሚለው የኢራን ወገኖች ይገባኛል ጥያቄ ስህተት መሆኑን የአሜሪካ ባለስልጣናት ተናግረዉ፤ ሁኔታው ተለዋዋጭ መሆኑን እና አስፈላጊ ከሆነ ጥቃቶቹ ዳግም ሊጀምሩ እንደሚችሉ ጨምረው ገልጸዋል።

ሳራ ዮሐንስ

ሐምሌ 03/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *